Grenfell Communications Amharic
Overview
ማጠቃለያ
የቤቶች፣ ማህበረሰቦችና የአካባቢው አስተዳደር ሚኒስቴር (Ministry of Housing, Communities, and Local Government (MHCLG)) ለግሬንፌል ታወር (Grenfell Tower) አሳዛኝ ሁኔታ ምላሽ የሚመራ የመንግስት መምሪያ ነው። እኛ፦
- ለግሬንፌል ታወር ጥያቄን እና የሕንፃ ደህንነትን፣ የእሳት ደህንነትን እና መጠነ ሰፊ ሪፎርሞችን ለማሻሻል የምንሰራ የመንግስትን ምላሽ እንመራለን።
- በግሬንፌል ታወር አሳዛኝ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ሁሉ መረጃን እና ዝማዎችን የማጋራት እና የሁለት መንገድ ውይይት የማድረግ ሃላፊነት አለብን።
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና የእሳት እና የሕንፃ ደህንነት ሚኒስትሩን ከግሬንፌል ማህበረሰብ ጋር ባላቸው ግንኙነት እንደግፋለን።
- በማህበረሰቡ የሚወሰን ተቀባይነት ያለው እና ዘላቂ የሆነ መታሰቢያ ለመወሰን ገለልተኛውን የግሬንፌል ታወር መታሰቢያ ኮሚሽንን እንደግፋለን።
- እርስዎ ትኩረት በሚሰጧቸው ጉዳዮች ላይ የግሬንፌል ማህበረሰብ ድምፆች በመንግስት ሁሉ እንዲሰማ ለማድረግ እንሰራለን።
- ከመላው መንግስት እና ከአካባቢው ካውንስል፣ ከአካባቢው NHS አገልግሎቶች እና ሎሎችም ጋር በመስራት የሚያስፈልግዎን ድጋፍ ማግኘትዎን እናረጋግጣለን።
- ሁሉም ስራዎች በጥንቃቄ እና በአክብሮት መከናወናቸውን እንዲሁም በሚከተሉት መንገዶች በእያንዳንዱ ሂደት ውስጥ ማህበረሰቡን ማሳተፋቸውን በማረጋገጥ የግሬንፌልድ ታወር ጣቢያ ደህንነት እና ጥበቃን እናስተዳድራለን፦
- በ Gov.uk ላይ የታተሙ ስለ ጣቢያው ወርሃዊ ዝማኔዎች
- ስለ ቁልፍ ጉዳዮች የማህበረሰብ ዝማኔዎች
- በ GOV.UK ላይ የታተሙ ሪፖርቶች እና መረጃ
የጊዜ አቆጣጠሮች
የግብረመልስ ቅጽ በጋውን በሙሉ ክፍት ሆኖ ይቆያል እና በመደበኛነት ምላሽዎችዎን እንገመግማለን። የእርስዎ እይታዎች ለመኸር እና ከዚያ
Why your views matter
የእርስዎ አስተያየቶች ለምን አስፈላጊ እንደሆኑ
የግሬንፌል ማህበረሰብን አሁን እና ለረጅም ጊዜ ለመደገፍ መንግሥት ቁርጠኛ ነው።
ስለ አሳዛኙ ሁኔታ ምላሽ ስለምንሰጥበት እና ቅድሚያ የሚሰጧቸውን እና ስጋቶችዎን ስለምንፈታበት ስራችን አዳዲስ መረጃዎችን እንዴት መቀበል እንደሚመርጡ በቀጥታ ከእርስዎ ዘንድ ልንሰማ እንፈልጋለን።
ሀዘን ላይ ያለ የቤተሰብ አባል፣ ከአደጋው የተረፈ ሆነ በቅርብ ማህበረሰብ ውስጥ የሚኖሩ ቢሆኑ የግሬንፌል ማህበረሰብ አካል ከሆኑ፣ እባክዎ ከታች ባለው አገናኝ ፈጣን የግብረመልስ ቅፅን በመሙላት በመሙላት አስተያየትዎን ያጋሩ።
Share
Share on Twitter Share on Facebook